press release
ለሚመለከተው ሁሉ ድርጅታችን አዲስ ፓዝ ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማህበር በስሩ ለሚገኙት የሽያጭ ማዕከላት በተለያዩ ጊዜያት ምርቶችን ከአቅራቢዎች በመረከብ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። በዚህም ካሉት የሽያጭ አውታሮች በተጨማሪ በድርጅቱ ድረ-ገጽ ምርቶቹን ለደንበኞቹ በማቅረብና ካሉበት ቦታ ሆነው ግዢአቸውን እንዲያከናውኑና ለግዢ የሚያጠፉትን ጊዜ እንዲቆጥቡ አመቻችቶ እየሰራ ይገኛል። በዚህም ከአብዛኛዎቹ ባንኮች ጋር፣ ከቴሌ ብር እና ከሌሎች Fintech ኩባንያዎች ጋር ጥምረትን በመፍጠር የክፍያ መንገዶችን...